Clean Diesel የጭነት መኪና የቪዲዮ ስልጠና

ወደዚህ በኢንተርኔት ላይ በቀጥታ ወደሚሰጠው ትምህርት እንኳን ደህና መጡ። በዚህ ተከታታይ ቪዲዮዎች ውስጥ፣ የጭነት መኪናዎን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እና አቅሙን ለማሳደግ እንዲችሉ clean diesel ሞተሮች ውስጥ ደቂቅ ነገርን ከውስጡ ለማውጣት እርዳታ እናደርጋለን።

አዲሶቹ የጭነት መኪኖች የናፍጣ ብክለትን ለመከላከል ቴክኖሎጂዎች አላቸው።  የናፍጣ ብክለት በሁሉም ሰው ላይ – በተለይም በዋናው መንገድ ላይ የሚኖሩ፤የሚሰሩ እና ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል።  ከአሮጌ የናፍጣ የጭነት መኪናዎች የሚወጣ ብክለት -እንደ አስም፤ የልብ በሽታ፤ካንሰር እና አካለ ጎደሎ ሆኖ መወለድን የመሳሰሉትን ከባድ የጤና ችግሮችን ያስከትላል።

የስልጠናው ማጠቃለያ 

ይህ የቪዲዮ ትምህርት clean diesel የጭነት መኪናዎን እንዴት መንከባከብ እንዳለብዎት፣ ውድ ዋጋ የሚያስወጡ ጥገናዎች እንዴት ማሰቀረት እንደሚችሉና ለነዳጅ የሚያወጡትን ወጪ እንዴት መቀነስ እንደሚችሉ ያሳያል። ትምህርቱ በሰባት ቪድዮዎች የተከፋፈለ ነው።

1.  የእርስዎን Clean Diesel ጭነት መኪኖችዎን መረዳት

ቁልፍ ነጥቦች

የጭነት መኪናዎ እንዴት እንደሚሰራ መረዳት ይህን ለማድረግ ያስችሎታል፡

 • ፍርሃትን ለማስወገድ ይረዳል
 • ገንዘብ ለመቆጠብ


2.  የClean Diesel የጭነት መኪኖችን  ልዩ የሚያደርጋቸው 5 መንገዶች

ቁልፍ ነጥቦች

Clean diesel የጭነት መኪኖች ከአሮጌ የጭነት መኪኖች በተለየ ሁኔታ ነው የሚሰሩት

 1. Idling ሞተሩን ይጎዳል
 2. የዳሽቦርድ መብራቶችም ችላ መባል የለባቸውም
 3. የሚያፈሱ ቀዳዳዎች ወዲያውኑ መጠገን አለባቸው
 4. ምቹ RPM የተለየ ነው
 5. ጥገና የበለጠ አስፈላጊ ነው


3.  Clean Diesel የጭነት መኪና የብክለት መቆጣጠሪያ መሳሪያ

ቁልፍ ነጥቦች  

DPF ስርአት ከ DEF ስርአት ሲነፃፀር 

DPF ስርአት

 • በ 2007 እና አዲስ ሞተሮች
 • ጥላሸት (soot) እና አመድ (ash) ይሰበስባል
 • አመድን ለማስወገድ በእጅ መፅዳት አለበት

DEF ስርአት

 • በ 2010 እና አዲስ ሞተሮች
 • ጭስ ማውጫውን በመቀየር ጎጂነቱን ይቀንሰዋል
 • DEF ፈሳሽ ይፈልጋል


4.  የነዳጅ መለያ ማጣሪያ (DPF) ሪጅንስ

ቁልፍ ነጥቦች

 1. የሞቀ የጭስ ማውጫ የጭነት መኪናዎን DPF ለማፅዳት ይረዳል
 2. የDPF መብራት በርቶ ከሆነ እርምጃ መውሰድ አለብዎ
  • ሞተሩ Active Regen እንዲፈጥር በኃይል ይንዱት (በምርጫነው)
  • ያ የማይሰራ ከሆነ Parked Regen ይጀምሩ
  • ያ የማይሰራ ከሆነ የጭነት መኪናዎ እንዲፈተሽ ያድርጉ


5.  DPF ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ የሞተር ክፍሎች

ቁልፍ ነጥቦች

 1. DPF ችግር እንዳይኖር ሞተሩን በጠቅላላ በመደበኛ ሁኔታ ያስጠግኑ
 2. DPF ላይ ተደጋጋሚ ችግሮች ያለብዎ ከሆነ የተቀረውን የሞተርዎን ክፍል ያረጋግጡ


6.  ገንዘብ ቆጣቢ ጥገና

ቁልፍ ነጥቦች

 1. ቀዳዳ የሚኖር ከሆነ እና የፈሳሽ አጠቃቀምን በተመለከተ ሁልጊዜ ሞተርዎን ይፈትሹ
 2. የሚከተሉትን ማወቅዎን ያረጋግጡ፡
  • የጭነት መኪናዎ የተለመደ የጥገና መርሀ ግብር
  • የጭነት መኪናዎclean diesel ሜካኒክ ሲያስፈልገው
 3. ማንኛውንም ችግር ወዲያውኑ ያስተካክሉ!


7.  DPF ማፅዳት እና መተካት

ቁልፍ ነጥቦች

DPF ማፅዳት እና መተካት

ሜካኒክ DPF ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ አፅድቷል ወይም ቀይሯል

ሜካኒክ የሚከተሉትን ማድረጉን እርግጠኛ ይሁኑ፡

 • DOC እና SCRተደፍኖ እንደሆነ ይፈትሻል
 • Parked Regen ማሮጥ
 • DPF Cleaning History Sheet ተሞልቷል (ለ DPF ማፅዳት ብቻ)

Reconditioned እና Aftermarket DPFs:

 • ርካሽ ናቸው
 • በአግባቡ ሊሰራም ላይሰራም ይችላል

እውቀትዎን ይፈትኑ

የእናንተን Clean Diesel የጭነት መኪና ምን ያህል እንደሚያውቁት ለማየት ይህንን ጥያቄዎች ይውሰዱት!

Start Test Amharic Opens in new window

የDPF1ፅዳት ቫውቸር ፕሮግራሙ ተዘግቷል፡፡  DPF ማጽጃ ቫውቸሮች ከአሁን በኋላ አይገኙም።

ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ በስልክ ቁጥር 206-689-4057 ወይም በኢሜይል bethc@pscleanair.org ያሳውቁ።

ምስጋና

Puget Sound Clean Air Agency በዚህ ተከታታይ ክፍል ያለው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ የሚታዩት የጭነት መኪና ሾፌሮች፣ ከባድ የጭነት መኪና ጥገናን በተመለከተ ቴክኒካዊ እውቀታቸውን lላበረከቱ  ግለሰቦች እና ይህንን ተንቀሳቃሽ ምስል በመተርጎም ድጋፍ ያደረጉ የማህበረሰብ አባላትን ጨምሮ ለዚህ የስልጠና ተንቀሳቃሽ ምስል ዝግጅት ስኬት እርዳታ ያደረጉትን    ሁሉንም ሰዎች ማመስገን ይፈልጋል፡፡

የኃላፊነት ማስተባበያ

Puget Sound Clean Air Agency የተወሰኑ የምርት ስሞችን ወይም ምርቶችን አያፀድቅም፡፡  በዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ የሚታዩት የምርት ስም ያላቸው ሁሉም ምርቶች እንደ መማሪያ ምሳሌዎች ብቻ የቀረቡ ሲሆን በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ መካተታቸው በPuget Sound Clean Air Agency በተዘዋዋሪ ለምርቱ እውቅና መስጠት አይደለም፡፡